በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ በትግራይ ጉብኝት አደረጉ

የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጄኮብሰን ዛሬ ተገናኝተው መነጋገራቸውን አስታወቁ።

በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተመሠረት ልዑካን ቡድኑ ትግራይ ክልል ሲገኝ ሁለተኛው መኾኑን በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት አቶ ጌታቸው፣ እስከ አሁን ስለተደረገው መሻሻል እና ስለገጠማቸው ተግዳሮቶች ለቡድኑ ገለጻ ማድረጋቸውን አጋርተዋል።

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ምዕራብ ትግራይ የመመለሱ ሂደት ስለሚፋጠነብት፣ የኤርትራ መንግሥት በፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም ለይ ደቅኗል ያሉትን ፈተና፣ እንዲሁም በትግራይ እየተካሄደ ያለውን የወታደሮች ብተና እና አጋጥሟል ያሉትን የአቅርቦትችግር በተመለከተ ሁለቱ ወገኖች አጽንኦት ሰጥተው መነጋገራቸውን አቶ ጌታቸው አመልክተዋል።

በትግራይ ላልታለመለት ጉዳይ የዋለውን ዕርዳታ በተመለከተ የሚካሄደው ምርመራ ሂደትን በተመለከተ ለአሜሪካው ቡድን መግለጫ መስጠታቸውን፣ እስከ አሁን የደረሱበትን ግኝት በተመለከተ ማብራራታቸውን እና አጠቃላይ ውጤቱንም ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ እንዲሁም አጥፊዎችን ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ለቡድኑ መናገራቸውን አቶ ጌታቸው ጨምረው ገልጸዋል። አሜሪካ “እጅግ አስፈላጊ” ያሉትን ርዳታ ለክልሉ ማድረጓን እንደገና እንድትቀጥል መጠየቃቸውን አቶ ጌታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የሐሳብ ልዩነት ለማጥበብ የሚደረግ ዲፕሎማሲ አካል መኾኑን፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG