በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት ከ አምባሳደር ግርማ አስመሮም በአፍሪቃ ህብረት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪ


የኤርትራ ፕሬዘዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለሱማልያው እስላማዊ ነውጠኛ ቡድን ለአልሻባብ እገዛ ያደርጋሉ በሚል ክስ አዲስ ማዕቀብ በሀገራቸው ላይ እንዳይጣል ለመከላከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፊት ቀርበው ለማስረዳት ጥያቄ ማቅረባቸውን ዲፕሎማቶች እንደተናገሩ ተዘግቧል

በ Angola Press ዘገባ መሠረት፥ ኢትዮጵያ፥ አዲስ አበባ ውስጥ የመሪዎች ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት የቦንብ ጥቃት ለማድረስ በተጠነሰሰ ሤራ እጇ ነበረበት ስትል በመክሰስ በኤርትራ ላይ ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጣልባት ለበርካታ ወራት ስትጥር ቆይታለች። አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ ደግሞ፥ ኤርትራ የሱማልያ ተዋጊዎችን እያስታጠቀች ነው በማለት ኬንያ እየከሰሰቻት ባለችበት ሁኔታ፥ የፀጥታው ምክር ቤት አባል የሆኑት የአፍሪቃ ሀገሮች ናይጄሪያና ጋቦን፥ በኤርትራ የማዕድን ኢንዱስትሪና ዜጎቿ ከውጭ በሚልኩት ገንዘብ ላይ እገዳ እንዲደረግ ያረቀቁትን የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል ተብሏል።

አስመራ ግን የሚቀርቡባትን ክሶች ሁሉ አጥብቃ መቃወም ብቻ ሳይሆን የሀሰት ውንጀላዎች ናቸው ስትል ታስተባብላለች።

በነዚህ ዘገባዎችና ሌሎች እንዲሁም ኢትዮጵያና ኤርትራን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ አምባሳደር ግርማ አስመሮም በአፍሪቃ ህብረት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪን ጋብዘናል።

ያነጋገራቸው ሰሎሞን ክፍሌ ነው:

XS
SM
MD
LG