በዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ልዩ አምባሳደር ቤት ቫን ሻክ ወደ ኢትዮጵያ መጓዛቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አምባሳደሯ ከህዳር 29 እስከ ታሕሣስ ሁለት በአዲስ አበባ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ያመለከተው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከዓለም አቀፍ የፍትህ ተሟጋቾች እና ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ጋር እንደሚገናኙ ገልጿል።
መግለጫው አክሎ አምባሳደሯ በዋናነት በኢትዮጵያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ፣ የሽግግር ፍትህ እና ተጠያቂነትን የሚያበረታቱ ሥራዎችን ማስፋፋት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ይወያያሉ ብሏል።
አምባሳደር ቫን ሻክ፣ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕን ለማሳካት በወጣው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ለመወያየት፣ ዓለም አቀፉ የፀጥታ ጥናት ተቋም እና የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባዘጋጁት ጉባዔ ላይ ንግግር እንደሚያደርጉም ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም