በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች መገደላቸው ተነገረ

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የአማሮ ወረዳ አስተዳደር የኦነግ ታጣቂዎች ካምፕ እየገቡ ነው የተባለው መንግሥት እርምጃ መውሰድ ስለጀመረ የማታለያ ዘዴ ሲል ይከሳል፡፡

የ"ኦነግ" ልቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት መረጃው የለኝም ብለዋል፡፡

በቦታው ያለው የመከላከያ ሰራዊት በበኩሉ ጥቃት አድራሹ የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው ይላል፡፡

እስከአሁን በአካባቢው በተፈፀመ ጥቃት 78 አርሶ አደሮች መገደላቸውን ፣ ከ114 አካል ጉዳተኛ ሲሆኑ ከ21 ሺህ በላይ ዘጎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው መንግሥት ይናገራል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች መገደላቸው ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG