በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግንቦት 22 ከተገደሉት ከወይዘሮ አማረች ገላኔ ባለቤት ከአቶ ገልገሎ ኩይታ ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ


በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በተካሄደ በሳምንቱ ግንቦት 22 ወይዘሮ አማረች ገላኔ በአንድ ታጣቂ መገደላቸውንና ገዳዩ የአስርና የአስራ ሁለት ዓመት ሁለት ልጆቻቸውን ማቁሰሉን ግንቦት 26 መዘገባችን ይታወሳል። በዚያን እለት ዘገባችን የሟች ባለቤት አቶ ገልገሎ ኩይታ ወይዘሮዋ የተገደሉበትን ሁኔታና ማንነታቸውን ቢያረጋግጡልንም በዘገባችን ቅድሚያ የሰጠነው ባልና ሚስቱ አባልና የምርጫ ተወዳዳሪ የሆኑበት ፓርቲ፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ቃል አቀባይ አቶ ማሙሸት አማረ የሰጡንን መረጃ ከምርጫ ቦርድ መልስ ጋር ለማቅረብ ነበር።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዚያን እለትና በቀጠሉት ቀናት በተደጋጋሚ ላደረግነዉ ጥሪ መልስ ባይሰጠንም፥ ባለፈው ሳምንት ሰኔ 18 የግንቦት 21 ዘገባችን ትክክል ያለመሆኑን የጠቆመ ደብዳቤ ኮፒ አዲስ አበባ ላለው ዘጋቢያችን ሰጥቷል።

ምርጫ ቦርድ በጠቆመን መሰረት የደቡብ ኦሞ ምርጫ ዞን ሃላፊ አቶ ዳንኤል ከበደን ማነጋገራችንም ይታወሳል። ባለስልጣኑ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ማህተም ተደርጎበት ተላከልን ያሉት ደብዳቤ፣ ወይዘሮ አማረች የመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ድርጅት አባል አይደሉም፣ ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት የላቸውም፣ ከገዳያቸውም ጋር ጥላቸው የግል ነዉ የሚል ገለጻ እንደሰጡን ይታወሳል። በዚያ ዝግጅታችን ደብዳቤውን ጻፉ የተባሉትን የደቡብ ኦሞ ዞን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሰብሳቢ አቶ መላኩ ሃይሌንና የሟች ባለቤት አቶ ገልገሎ ኩይታን ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም።

ዛሬ ትዝታ በላቸዉ አቶ ገልገሎን በስልክ አግኝታ አነጋግራለች።

ቃለ-መጠይቁን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG