በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ ከተማ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ የሰዎች ህይወት ጠፋ


በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ትናንት በአጥፍቶ ጠፊ በደረሰ የቦንብ አደጋ 11 ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞችና ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ጥቃቱ የተፈፀመው የሞቃዲሾ የአየር ማረፊያና እና የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ዋጃሪ ወረዳ፣ የየሶማሌ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች ባቋቋሙት የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሻይ ቤት ውስጥ ነው።

ከሞቱት መሀከል ወታደሮችና ንፁሃን ሰዎች የሚገኙ መሆኑን ለሚዲያ መረጃ የመስጠት መብት እንደሌላቸው በመግለፅ ማንነታቸው እንዳይገለፅየጠየቁ የሶማሌ መንግስት ባለሥልጣን ተናግረዋል።

ለጥቃቱ የአል-ሻባብ ታጣቂ ቡድን ሀላፊነቱን ወስዷል።

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሞሀመድ ሁሴን ሮቤል አረመኔያዊ ያሉትን ጥቃት አውግዘው ይህ አልሻባብ ያለምንም ልዩነት የሶማሌን ህዝብ ደም የሚያፈስ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG