በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አልሻባብ 18 ሰዎች መግደሉ ተገለፀ


የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አልሻባብ ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ወዲህ አስራ ስምንት ሰዎች መግደሉ ተገለጠ።

በዩናይትድ ስቴትስ የአየር ጥቃት ተወጥሮ የሚገኘው ታጣቂው ቡድን ትናንት ዕሁድ በደቡባዊዋ ጃማሜ ከተማ የአልሻባብ ፍርድ ቤት የቀረቡ አራት ሰዎች ዳኛው ወንጀል ፈጽመዋል ብሎ ውሳኔ እንደሰጠ ወዲያውኑ ቅጣቱን ፈፅመዋል።

የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች ናቸው ተብለው የተወነጀሉ ሁለት ወንዶች እና ለኬንያ ትሰልላለች የተባለች የሀያ ዓመት ሴት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

ከዚያ በማስከተል የአስራ ስድስት ዓመት ሴት ልጅ አስገድዶ ደፍሩዋል የእስራ ስምንት ዓመት ወጣት በአደባባይ በድንጋይ ተወግሮ ተገድሏል። ተከሳሹ “አረ በስምምነት ነው” ብሎ ቢከራከርም ዳኛው በጊዜው ባለትዳር ሆነህ ይህን መፈጸምህ ሞት ይገባሃል ብሎ እንደፈረበት ተዘግቧል።

ቅዳሜ ዕለት ሳላግሌ በምትባል ከተማም ለሶማሊያ መንግሥት ለኬንያና ለዩናይትድ ስቴትስ የሥለላ ድርጅት ሰልላችኋል ያላቸውን አስር ወንዶች ረሽኗል።

በሰዎቹ ላይ የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው በጽንፈኛው ቡድን ፍርድ ቤቶች ሲሆን ጠበቃ እንዲቆምላቸው አልተፈቀደላቸውም። ታጣቂው ቡድን ሰዎቹ የተከሰሱበትን ወንጀል መፈጸማቸውን አምነዋል ቢሉም ነቃፊዎች ግን በድብደባ ብዛት እንደሆነ ይጠረጥራሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG