በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለወራት መሞታቸው ሲነገር የቆየው የአል-ቃይዳው መሪ በአዲስ ቪዲዮ ታይተዋል


የአል-ቃይዳ መሪ አይማን አል-ዛዋሪ
የአል-ቃይዳ መሪ አይማን አል-ዛዋሪ

ለወራት መሞታቸው ሲነገር የቆየው የአል-ቃይዳ መሪ አይማን አል-ዛዋሪ - የመስከረም 11ዱ ጥቃት 20ኛ ዓመቱን እየተከበረ ባለበት ወቅት በአዲስ ቪዲዮ ታይተዋል።

ሳይት የተሰኘ የጂሀዲስቶችን ድህረገፅ የሚቆጣጠረው የአሜሪካ የደህንነት ቡድን እንዳስታወቀው ቪዲዮው የተለቀቀው ቅዳሜ እለት ሲሆን - አል-ዛዋሪ "እየሩሳሌም መቼም የአይሁዳውያን መኖሪያ አትሆንም" ሲሉ ተሰምተዋል።

በተጨማሪምአል-ቃይዳ በ ጥር ወር ላይ የፈፀሙትን ሶሪያ ውስጥ የሚገኙ የራሽያን ወታደሮች ኢላማ ያደረገ ጥቃት እና ሌሎች ጥቃቶችንም አድንቀዋል።

አልዛዋዲ በመልክታቸው ከ20 ዓመታት በኃላ የዩናይትድ ስቴትስን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን መውጣት መጥቀሳቸውን ሳይት አስታውቋል። ሆኖም አፍጋኒስታንን የመልቀቁ ሂደት ከታሊባን ጋር ስምምነት ላይ የተደረሰው ባለፈው አመት የካቲት ላይ እንደመሆኑ ቪዲዮው አዲስ የተቀዳ ለመሆኑ አያመለክትም ሲል ሳይት ጨምሮ ገልጿል።

አል-ዛዋሪ ስለ ታሊባን ዳግም አፍጋኒስታንንና ዋና ከተማዋን ካቡል መቆጣጠራቸው ምንም አለመናገራቸውንም ሳይት አስታውቋል።

አልዛዋሪ እ.አ.አ በ2020 መጨረሻ አካባቢ በህመም ምክንያት መሞታቸው ሲነገር ከቆየ በኋላ እስከ ቅዳሜ እለት ድረስ በህይወት ስለመኖራቸው የሚገልፅ ምንም አይነት ቪዲዮም ሆነ ማስረጃ ሳይታይ ቆይቷል።

የአልዛዋሪ ንግግር 61 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ የሚፈጅ ሲሆን አልሻባብ ሚዲያ ፋውንዴሽን በተሰኘው ቡድን የተለቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG