በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የት/ቤት ምገባ ፕሮግራም ሕጻናትን ከረሃብ ታድጓል - የዓለም የምግብ ፕሮግራም


በቀን ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ሕጻናት እንዲያገኙ ለማድረግ መንግስታት በመከተል ላይ ያሉት ልጆችን በትምህርት ቤት የመመገብ ፕሮግራም እጅግ አስፈላጊና በወጪም ረገድ ውጤታማ እንደሆነ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በዓለም ግማሽ የሚሆኑት ተማሪ ልጆች በትምህርት ቤታቸው ምግብ በማግኘት ላይ እንደሆኑና፣ ለምግብ እጥረት እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ሊሎች በርካታ ልጆች ግን ለዛ እንዳልታደሉ የምግብ ፕሮግራሙ በመግለጫው አመልክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዛሬ ባወጣውና በትምህትርት ቤቶች ህጻናትን መመገብን በተመለከተ ይፋ የሆነው ሪፖርት እንዳመልከከተው በዓለም አቀፍ ደረጃ 420 ሚሊዮን ህጻናት በትምህርት ቤታቸው ምግብ ያገኛሉ።

153 ሚሊዮን ሕጻናትን ጨምሮ 345 ሚሊዮን ሰዎች ረሃብ በተጋረጠባቸው በዚህ ወቅት የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሙ ከፍተኛ ችግር ያለባቸውን ሕጻናት ታድጓል ብሏል ሪፖርቱ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮራም 50 ቢልዮን ዶላር እንደሚፈጀ ያመለከተው ሪፖርት በእአአ 2030 ሁሉንም የትምህርት ቤት ሕጻናት ለመመገብ በተያዘው ዕቅድ ውስጥ 75 መንግስታት ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል ብሏል።

XS
SM
MD
LG