በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን 80 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች ተመረዙ


ሴት ተማሪዎች በትምህር ላይ ካቡል፣ አፍጋኒስታን
ሴት ተማሪዎች በትምህር ላይ ካቡል፣ አፍጋኒስታን

ታሊባን ጺም መላጨትን አገደ

በሰሜን አፍጋኒስታን 80 የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሴት ተማሪዎች ተመርዘው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአካባቢው የትምሕርት ሃላፊዎች አስታውቀዋል።

ታሊባን በአፍጋኒስታን ስልጣን ከተቆጣጠረና በአገሪቱ ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የመብት እገዳ ከጣለ ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ታውቋል።

ታሊባን በአፍጋኒስታን ልጃገረዶች ከስድስተኛ ክፍል በላይ እንዳይማሩ ሲያግድ፣ ሴቶች ከሥራም ሆነ ከአብዛኛው የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ታግደዋል።

የመርዝ ጥቃቱን የፈጸመው ግለሰብ በቂም ተነሳስቶ መሆኑን ያስታወቁት ባለሥልጣናት፣ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ወደ 80 የሚጠጉት ሴት ተማሪዎች የተመረዙት ቅዳሜ እና እሁድ ለየብቻ በተፈጸሙ የመርዝ ጥቃቶች ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምዕራብ አፍጋኒስታን የሚገኙ የወንዶች ጸጉር ቤቶች ጺም እንዳይላጩ ወይም እንዳያስተካክሉ እገዳ ተጥሏል።

ከሻሪያ ውይም ከእስልምና ትዕዛዝ ያፈነገጠ ነው በሚል ታሊባን የጣለው እገዳ፣ በጸጉር ቤቶቹ እና ጺማቸውን መላጨት በሚያዘትሩት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።

ታሊባን ከ 20 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ከስልጣን ከተወገደ በኋላ፣ ጺም መላጨት እና መከርከም በአገሪቱ በብዛት ተዘውትሮ ነበር። ከሁለት ዓመታት በፊት መልሶ ስልጣኑን ሲቆጣጠር እገዳው ተመልሶ ተግባራዊ ሆኗል።

XS
SM
MD
LG