በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ ተያዘ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ

የጣሊያን ፖሊስ ከአውሮፓ ህብረት ፖሊስ፣ ከብሪታኒያና ኔዘርላንድስ ፖሊሶችና ከዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተፈላጊ የነበረውን ኤርትራዊ ገ/መድህን ተመስገን ገብሩን ትናንት ማክሰኞ አዲስ አበባ ላይ መያዙን አስታውቋል፡፡

የሰላሳ አምስት ዓመቱ ገ/መድህን የተያዘው በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በአውስትራሊያ ፓስፖርት ወደ አውስትራሊያ አደሌድ ከተማ በሚጓዝ አውሮፕላን ተሳፍሮ ሊሄድ ሲሞክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ገ/መድህን የታሰረው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ስደተኞችን በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን፣ ብሪታኒያ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ቤልጂየም እና ኔዘርላንድስ በህገወጥ መንገድ በማስተላለፍ ወንጀል መሆኑን የጣሊያን ፖሊስ ተናግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG