በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

​አልጄሪያ በዓለም ሦስተኛውን ትልቅ መስጅድ አስመረቀች


አልጄሪያ በዋና ከተማዋ በአልጀርስ አዲስ ያስገነባችውንና በግዙፍነቱ በዓለም ሦስተኛ የሆነውን መስጂድ
አልጄሪያ በዋና ከተማዋ በአልጀርስ አዲስ ያስገነባችውንና በግዙፍነቱ በዓለም ሦስተኛ የሆነውን መስጂድ

አልጄሪያ በዋና ከተማዋ በአልጀርስ አዲስ ያስገነባችውንና በግዙፍነቱ በዓለም ሦስተኛ የሆነውን መስጂድ ትናንት ዕሁድ አስመርቃለች።

የመንግሥቱን ጥንካሬና ሀይማኖታዊ ተምሳሌት መገለጫ ሆኖ የተጀመረው መስጂድ የተጠናቀቀው ከረጅም ጊዜ የፖለቲካ ውጣ ዉረድና ከተገመተው በላይ ብዙ ገንዘብ ካሰወጣ በኋላ ነው፡፡

የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ በገቡት ቃል ቃል መሠረት ያስገነቡትን መስጂድ የመረቁት በታላቅ ድምቀት እና ሥነ ሥርዓት ነው፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2010 በኋላ በነበሩት አሥርት ዓመታት ውስጥ በቻይና የግንባታ ድርጅት የተገነባው “ታላቁ የአልጀርስ መስጂድ” 265 ሜትር ከፍታ ያለው በዓለም ላይ ካሉት ሁሉ ረጅሙ ህንጻ (ሚናራ) ያለው ነው።

ከእስልምና ሓይማኖት ቅዱስ ከተሞች ውጭ ትልቁ ነው የተባለው ይህ መስጂድ በትልቅነቱ ከዓለም ሶስተኛው ሲሆን 120,000 ምእመናን ሊያስተናግድ የሚችል ትልቅ የመስገጃ ስፍራ እንዳለው ተነግሯል፡፡

በዘመናዊ የኪነ ህንጻ ንድፍ የተገነባው መስጂድ የአልጄሪያን ባህል ለማክበር የአረብ እና የሰሜን አፍሪካ እድገትን እንዲያሳይ ሆኖ የተሠራ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

እስከ አንድ ሚሊዮን መጻህፍትን መያዝ የሚችል ቤተ መፃህፍት ያለው ሲሆን የሂሊኮፕተር ማረፊያም አለው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG