በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቴሌቭዥን ጥያቄና መልስ “ጄፐርዲ” አስተናጋጅ አሌክስ ትሪቤክ አረፈ


ፎቶ ፋይል፦ የጄፐርዲ አስተናጋጅ አሌክስ ትሪቤክ
ፎቶ ፋይል፦ የጄፐርዲ አስተናጋጅ አሌክስ ትሪቤክ

የጄፐርዲ አስተናጋጅ አሌክስ ትሪቤክ በሰማኒያ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አሌክስ ትሪቤክ ትናንት ዕሁድ ህይወቱ ያለፈው ለሁለት ዓመታት ያህል በጣፊያ ካንሰር ምክንያት ታሞ ከቆየ በኋላ ነው።

ተወዳጁን የጠቅላላ ዕውቀት የቴሌቭዥን ዝግጅት ከሠላሳ ዓመታት በላይ ያስተናገደው አሌክስ ትሪቤክ ከተወዳዳሪዎቹ ጋር በሚያደርጋቸው ቀልድ የተላበሱ ጭውውቶች፣ ለጥያቄዎቹ ትክክለኛ መልስ በሚሰጡበት ጊዜ በሚታይበት ዕውነተኛ ደስታ እንዲሁም መልሱን አጥተው ሲቸገሩ ቀልጠፍ ብሎ ወደቀጣዩ በማሻገር ጥበቡ ፕሮግራሙን ለከፍተኛ ተወዳጅነት ያበቃ አስተናጋጅ ነበር።

ካናዳ ተወላጁ አሌክስ ትሬቤክ የጥያቄና መልስ ውድድር ሙያውን የጀመረው በትውልድ ሃገሩ በካናዳ "ሪች ፎር ዘ ታፕ" በተባለ ፕሮግራም ሲሆን ኑሮውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው እአአ በ1973 ነበር።

XS
SM
MD
LG