በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ በታጣቂዎች ጥቃት ሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ


የዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ
የዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኘው የዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እና ትላንት ሰኞ፣ ለዘረፋ የተደራጁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት፣ አንድ ሰው መገደሉንና 10 ሰዎች መቁሰላቸውን ስደተኞች ተናገሩ፡፡

ስደተኞቹ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ምሽት ታጣቂዎች ወደ መጠለያው ገብተው፣ ስምንት ሰዎችን በስለት ወግተው ማቁሰላቸውን ተናግረዋል፡፡ ትላንት ሰኞ በተፈጸመ ጥቃት ደግሞ፣ የሰው ሕይወት ማለፉንና የቆሰሉም መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ በታጣቂዎች ጥቃት ሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00

መጠለያ ጣቢያው የሚገኝበት የዳባት ወረዳ የጭላ ቀበሌ አስተዳደር በበኩሉ፣ በሁለቱም ቀናት በተፈጸሙት ጥቃቶች፣ አንድ ሰው መገደሉንና የተጎዱም እንዳሉ አረጋግጦ፣ የመጠለያ ጣቢያውን ጸጥታ ለማስከበር እየሠራ መኾኑን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎትም፣ የመጠለያ ጣቢያውን ጥበቃ ለማጠናከር እየሠራ እንደኾነ አስታውቋል፡፡ በየደረጃው ካሉ ሌሎች የመንግሥት አስተዳደር አካላት ተጨማሪ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG