ዋሺንግተን ዲሲ —
በአልቤንያ በደረሰው ርዕደ መሬት ከሞቱት መካከል ልጆች እንደሚገኙባቸው ታውቋል። ቢያንስ 12 በወደብ ከተማ ዱሬስ፣ በትንሹ 14 ቱማኔ፣ ቢያንስ አንድ ሰው ደግሞ ኩርቢን በተባሉት ከተሞች እንደሞቱ ተገልጿል። አሁንም የገቡበት ያልታወቀ ሰዎች ስላሉ የሙታኑ ብዛት ሊጨምር እንደሚችል ባለሥልጣኖች ገልፀዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።
የመድህን ሰራተኞች ሰዎችን ከፍርስራሾች ለማውጣት እየጣሩ ነው። መንግሥት እጅግ በተጎዱት አከባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር አውጇል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ