በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት የተካሔደባቸው የራያ አላማጣ ቀበሌዎች መረጋጋታቸውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ


ግጭት የተካሔደባቸው የራያ አላማጣ ቀበሌዎች መረጋጋታቸውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:45 0:00

ግጭት የተካሔደባቸው የራያ አላማጣ ቀበሌዎች መረጋጋታቸውን ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ

ፌደራል መንግሥቱ “አከራካሪ” ሲል በሚገልጻቸውና የትግራይ እና የአማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሡባቸው አካባቢዎች አንዱ በኾነው በራያ አላማጣ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች፣ ባለፈው ረቡዕ ምሽት፣ በትግራይ ክልል የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው ሚሊሻ መካከል ከተካሔደው የተኩስ ልውውጥ በኋላ “አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል” ሲል፣ የአላማጣ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታውቋል።

ከአላማጣ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰነዘረውን ውንጀላ አስመልክቶ፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ቃል አቀባይ ረዳዒ ኃለፎም ምላሽ ለማግኘት፣ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የአማራ ክልልም ኾነ የፌደራሉ መንግሥት፣ እስከ አሁን በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት የለም። የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ግን፣ የአከራካሪ ቦታዎችን ኹኔታ በዘላቂነት ለመፍታት፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናነት ከሚመለከታቸው “ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር” ተብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG