በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በራያ አላማጣ ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ


በራያ አላማጣ ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

በራያ አላማጣ ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ

የራያ ማንነት ጥያቄ፣ በሕዝበ ውሳኔ እልባት እንዲሰጠው መንግሥት ያስቀመጠው አቅጣጫ እንዲተገብር የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ በአላማጣ ከተማ ተካሔደ፡፡

“መንግሥት ከሕዝብ ጋራ ባደረገው ውይይት፣ በአካባቢው ጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደር እንደሚቋቋም አረጋግጧል፤” ያሉት ሰልፈኞቹ፣ ኾኖም፣ ይህ ሳይተገበር ወር እንዳለፈው አመልክተዋል፡፡

ዞኑ፣ ከሦስት ዓመት በላይ፣ ምንም ዓይነት በጀት ከመንግሥት እንዳልተመደበለት ሰልፈኞቹ አስታውሰዋል፡፡ ይህም፣ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴው ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ አስረድተዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሓላፊ ረዳኢ ኃለፎም፣ “የሽግግር አስተዳደር ጥያቄውም ኾነ፣ ጥያቄው እንዲተገበር የሚደረጉ ግፊቶች፣ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ናቸው፤” ሲሉ ተችተዋል፡፡ “ጥያቄውም መቅረብ ያለበት ለትግራይ ክልል ነው፤” ሲሉም ይከራከራሉ፡፡

የአላማጣ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ከንቲባ ግን፣ ለትግራይ ክልል ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ፣ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት ይግባኝ ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG