ዋሺንግተን ዲሲ —
ሶማሊያ የታችኛው ጁባ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ዛሬ ሰኞ ማለዳ የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት አድርሰው ቢያንስ አሥራ ሁለት ሰዎች ተገደሉ።
አልሻባባ በጥቃቱ ዒላማ ያደረገው ከኪስማዮ ከተማ ሃምሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ መሆኑን የሶማሊያ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ የሶማሊእና አገልግሎት ገልፀዋል።
አልሸባብ ካምፑን ወርረን ሃያ ሰባት የመንግሥት ወታደሮች ገድለናል ያለ ሲሆን የመንግሥቱ ባለሥልጣን መሰረተ ቢስ ሲሉ አስተባብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ