በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአል ሻባብ አማጽያን ሶማልያ ሞቅዲሾ የሚገኝ ወታደራዊ የጦር ካምፕ ወረሩ

የአል ሻባብ አማጽያን፣ ዛሬ ዐርብ ቦምብ በጫነ የአጥፍቶ ጠፊ መኪና ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ የሚገኝ ወታደራዊ የጦር ካምፕ መውረራቸውና ጥቃት ማካሄዳቸው ተገለፀ።

የአል ሻባብ አማጽያን፣ ዛሬ ዐርብ ቦምብ በጫነ የአጥፍቶ ጠፊ መኪና ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ የሚገኝ ወታደራዊ የጦር ካምፕ መውረራቸውና ጥቃት ማካሄዳቸው ተገለፀ።

የታቸኛው ሸበሌ ክልል ገዢ ኢብራሂም አደን ናጃህ ለቪኦኤ ሶማልኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ አማጽያኑ ጥቃቱን ያካሄዱት ከሞቅዲሾ ደቡብ ምዕራብ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለችው ባሪር ከተማ ላይ ነው።

የመንግሥቱ ኃይሎች፣ አማጽያኑ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ተኩል ገደማ የጀመሩትን ጥቃት መመለስ ቢችሉም፣ አማጽያኑ ሌላ ጥቃት ጀምረው ከባድ ውጊያ መካሄዱንም፣ እኒሁ የሸበሌ ገዢ አስታውቀዋል።

አል ሻባብ ጥቃቱን እንዳካሄደና 11 ተሽከርካሪዎችም እንደማረከ አምኗል፣ ሮይተርስ እንደዘገበው ደግሞ 15 ወታደሮች ተገድለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG