እስካሁን ባለው ጊዜ ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወገን እንደሌለ ሚቲጋ አውሮፕላን ማረፍያ ላይ ያሉት የጸጥታ መኮንኖች ገልጸዋል። አይሮፕላን ማርፈያው የተደበደበው ማኮብኮብያው ጎዳና ላይ ሲሆን በሰዎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ተገልጿል።
የወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ኻሊፋ ሃፍታር ታማኝ ወታደሮች መዲናዋን ትሪፕሊን ለመቆጣጠር እየገፉ ናቸው።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፉት፣ የሊብያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋየዝ ሳራጅ የሀፍታርን ተግባር የመፈንቀለ መንግሥት ሙከራ ነው ብለዋል። ሀፍታርና ቡድናቸው ከትሪፕሊ ወጣ ብለው በሚገኙት አካባቢዎች ሲገፉ ቆይተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ