በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእርዳታ ፖሊሲና የሰብዓዊ ደንቦች ፖለቲካ


ድንበር የለሽ ሐኪሞች በአጣዳፊ ደራሽ እርዳታ ግንባር
ድንበር የለሽ ሐኪሞች በአጣዳፊ ደራሽ እርዳታ ግንባር

የረድዔት ድርጅቶች የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ሰለባዎችን ለመታደግ ሲሞክሩ ብዙ ጊዜ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ይዘገባል።

በተለይ ለበረታ ችግር የተጋለጡ ማህበረሰቦችን ፈጥነው ለመድረስ ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ሲደራደሩ፥ በሥነ ምግባር ጥያቄ ዙሪያ አዕምሮን የሚረብሹ ሁለት ክፉ ምርጫዎች ይቀርቡላቸዋል። ሕይወት ለማትረፍ በሚያደርጉት ጥረት አንዱን መምረጥ ይገደዳሉ።

Medecins sans Frontieres (ድንበር የለሽ ሐኪሞች) የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ባለፉት 40 ዓመታት የገጠሙትን አንዳንድ ችግሮች ባለፈው ሣምንት በበርሊን ጉባዔው ላይ መርምሯል።

"የእርዳታ ፖሊሲና የሰብዓዊ መብቶች ፖለቲካ በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና በጉባዔው ላይ የቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ በመጭው ኅዳር ወር አጋማሽ ላይ በይፋ ይመረቃል፡፡

መፅሐፉን በጋራ ካዘጋጁት አንዱ ፋብሪስ ዋይስማን ይባላሉ፡፡

"ሰብዓዊ ድርጅቶች ብዙውን ጊዜ እኛ ከፖለቲካ በላይ ነን ብለው ይናገራሉ፡፡ ያ ግን ፈፅሞ ትክክል አይደለም" ይላሉ፡፡

"አሁንም በዋናነት የምንከተለውን መመሪያ እንጠብቃለን፤ ያም ዐብይ እምነታችን ሕይወት ማዳን ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን አንዳንድ መሠረተ ቢስ እምነቶችን ደግሞ ለማስወገድ እንጥራለን፡፡ በዚህም 'ድንበር የለሽ ሐኪሞች መቼ ነው የራሱን አሣልፎ መስጠት ያለበትና የሌለበት?' የሚለውን ትልቁን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራል፡፡" ሲሉ ዋይስማን አክለው ያስረዳሉ፡፡

ለረድዔት ድርጅቶቹ ገንዘብ የሚያዋጡ ወገኖች በበኩላቸው ብዙውን ጊዜ ሰብዓዊ ደንቦች በሚል ሽፋን ለሚሰጠው መግለጫ ሣይሆን የፖለቲካውን ውል የሥልጣንና ፍላጎቶችን ሚዛን ጠብቆ የርዳታውን እንቅስቃሴ ወደፊት ማራመድ የሚቻልበትን መንገድ ለመመርመር በርካታ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

ጉባዔው በዋናነት የመከረባቸውን እንጠቃቅሣለን፡፡

ዝርዝሩን ከሰሎሞን ክፍሌ ጥንቅር ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG