በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ትግራይ ክልል ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተሽከርካሪዎች መመለሳቸውን መንግሥት አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ
ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ

ባለፈው ሳምንት የእርዳታ ቁሳቁሶችን ጭነው ወደ ትግራይ ክልል ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተሽከርካሪዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ከመንገድ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ፣ ተሸከርካሪዎቹ የህወሓት ታጣቂዎች የአባላ መስመርን ዘግተው በከፈቱት ተኩስ ምክንያት ጉዟቸውን አቋርጠው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል በውጭ ግንኙነት ቢሮ አስተባባሪ መሆናቸውን የሚናገሩትና በካናዳ የሚገኙት አቶ ዩሃንስ አብርሃ ወደ ትግራይ የተንቀሳቀሱ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ ተሸከርካሪዎች እንደሌሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ለገሰ ጉዞ ጀምረው የተመለሱት ተሽከርካሪዎች የየትኛው ድርጅት እንደሆነ ባይገልጹም፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች በፀጥታ ሥጋት ምክንያት ከሰመራ እንዳልተነሱ ተቋሙ ለቪኦኤ ገልጿል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ወደ ትግራይ ክልል ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተሽከርካሪዎች መመለሳቸውን መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:34 0:00

XS
SM
MD
LG