በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶች እንቅስቃሴ መታገድ በኢትዮጵያ


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

ሁለት ዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ የምናደርገውን እንቅስቃሴ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አግዶብናል ሲሉ አስታወቁ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ዋን ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በትግራይ ክልል እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚሰሩ የረድኤት ሰራተኞችን በጅምላ መወንጀላቸው አደገኛ ተግባር በመሆኑ መቆም አለበት በማለት ማስጠንቀቃቸውን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ድንበር የለሽ ሃኪሞች እና ኖርዌጂያን የስደተኞች ካውንስል የተባሉት የእርዳታ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ዐርብ እአአ ሃምሌ 30 ቀን እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ ዕገዳ እንደጣለ አስታውቀዋል።

የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ቃል አቀባይ ለዕገዳው የተሰጠው ምክንያት "በይፋ የተሟጋችነት አድራጎት መፈጸም" የሚል እና የውጭ ሃገር ዜጎች ለሆኑ ሰራተኞቻችሁ ተገቢውን የስራ ፈቃድ አላወጣችሁም የሚል መሆኑና እንቅስቃሴዎቹ በሙሉ መታገዳቸውን እንዳስታወቀ አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን ቃል አቀባይ በበኩሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰማራው የሆላንዱ የድርጅቱ ቅርንጫፍ የእርዳታ እንቅስቃሴ ከሁሉም ግዙፉ መሆኑን ጠቅሶ በትግራይ፣ አማራ፣ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች እንቅስቃሴዎቻችን ለሦስት ወራት ታግደውብናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠን እየጠየቅን ነን ብሏል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ ማጣሪያ ግብረ ሃይል ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ክልሉ ግጭት በተያያዘ የረድኤት ድርጅቶች የትግራይ ተዋጊ ሃይሎችን ማስታጠቅን ጨምሮ አፍራሽ ሚና እየተጫወቱ ናቸው በማለት ወንጅለው እንደነበር ኤፒ ጠቅሶ በሁለቱ የእርዳታ ድርጅቶች መታገድን በተመለከተው ጉዳይ የአምባሳደር ሬድዋንን ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ አክሏል።

የተመዱ የሰብዓዊ ጉዳዮች እና የአጣዳፊ እርዳታዎች ምክትል ዋና ጸኃፊ ማርቲን ግሪፊዝ እንዲህ ያሉ የጅምላ ውንጀላዎች መሰንዘር ትክክል አይደለም። በማስረጃ መደገፍ አለበት ማለታቸውን ኤፒ ጠቅሷል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በበኩሉ ከተቋቋሙለት ዓላማ ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሦስት የተራድኦ ድርጅቶችን ማገዱን አስታውቋል።

የታገዱት ድርጅቶችም አንደኛ ኤምኤስኤፍ ሆላንድ፣ ኖርዌጂያን ሬፊዩጂ ካውንስል እና አል ማኽቱም ፋውንዴሽን የተባሉ የውጭ ድርጅቶች የኢትዬጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰጣቸው ፍቃድ በህጋዊነት በተለያዩ የሰብዓዊ ስራዎች ተሰማርተው እየሰሩ የቆዩ ድርጅቶች ሲሆኑ የድርጅቶቹን እንቅስቃሴ በተመለከተ ፍቃድ ሰጪው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሚያደርገው ክትትል መሰረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት ዓላማ ውጭ በመንቀሳቀሳቸው መሆኑን ማስታወቁን የኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG