በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለማቀፉ የረድዔት ድርጅቶች ለየመናዊያን ዕርዳታ ለማቅረብ መቸገራቸውን ገለፁ

በየመን የወደብ ከተማ ሆዴዳ ውስጥ በመንግሥቱ ወታደሮችና በሽምቅ ተዋጊች መካከል ባለ ፍጥጫ አጣብቂኝ ውስጥ ለሚገኙ የመናውያን ዕርዳታ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ዓለማቀፉ የረድዔት ድርጅት መተላለፊያ ኮሪዶር መጠየቁ ተገለፀ።

በየመን የወደብ ከተማ ሆዴዳ ውስጥ በመንግሥቱ ወታደሮችና በሽምቅ ተዋጊች መካከል ባለ ፍጥጫ አጣብቂኝ ውስጥ ለሚገኙ የመናውያን ዕርዳታ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ዓለማቀፉ የረድዔት ድርጅት መተላለፊያ ኮሪዶር መጠየቁ ተገለፀ።

መንግሥታዊ ያልሆነው የረድዔት ድርጅት ሴቭዘቺልድሬን እንደገለጸው፣ በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ግጭት ምክንያት፣ ከክሊኒኮቹ አንዱ ውድመት ደርሶበታል። ይህ ፍልሚያ የሚካሄድበት የሆዴዳ ቀይ ባሕር ከተማ፣ ወደ 600,000 ያህል ሕዝብ መኖሪያ መሆኑም ተመልክቷል።

በዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መግለጫ መሠረትም፣ ከከተማው ትልቁ ሆፒታል የሚገኘው፣ ጦርነቱ የሚካሄድበት ግንባር ላይ ነው።

የዩኒሴፍና የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቃል አቀባዮችም፣ በመንግሥቱና በሽምቅ ተዋጊዎቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነት፣ ሲቪሉ ማኅበረሰብ ከሚኖርበት አካባቢ የተቀራረበ ከመሆኑም በላይ፣ ለዕርዳታ አቅርቦቱም በጣም አስቸጋሪ ሁኔታን እንደፈጠረ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG