በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን እህል የምትልክበት መተላለፊያ ጊዜ ገደብ ማብቃቱ ስጋት ፈጥሯል


ሠራተኞች ኢዝሜል ወደብ ዩክሬን እህል እየጫኑ እአአ ሚያዚያ 26/2023
ሠራተኞች ኢዝሜል ወደብ ዩክሬን እህል እየጫኑ እአአ ሚያዚያ 26/2023

ዩክሬን የእህል ምርቷን ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መተላለፊያ መንገድ የሚፈቅደው ስምምነት ተግባራዊነት ማብቃቱን፤ ሩሲያ ማስታወቋ ስጋትን ፈጥሯል። የዓለም አቀፉ የነፍስ አድን ኮሚቴ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሻሽዋት ሳራፍ፣ በአለም አቀፍ የምግብ ገበያዎች ላይ "አለመረጋጋት እና የግብይት ቀውስ" ይፈጥራል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አክለውም “የዋጋ ንረት ሊጨምር እና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሰብል ውድመት እና የእንሣት እልቂት በገጠማቸው ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ሀገራት የምግብ ዋስትና ማጣትን ከፍ ሊያደርግ ይችላል” ብለዋል።

የተቋረጠው ስምምነት እንዲቀጥል ካልተደረገም፣ አጠቃላይ በምርት እና በምግብ ገበያዎች፣ በተለይም እንደ አፍጋንስታን፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ እና ሱዳን በመሳሰሉ አገሮች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ተናግረዋል።

ለምሳሌም ያህል ‘ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ከዩክሬን የሚያስመጧቸው የእህል ምርቶች ወሳኝ ናቸው’ ሲሉም ኃላፊው አክለዋል።

በሌላ በኩል፣ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንዳሉት ‘ሩሲያ የራሷን ምግብ እና የማዳበሪያ ምርቶች ለዓለም ገበያ ማቅረብ የመቻል ፍላጎቷ እስኪሟላ ድረስ “የጥቁር ባህር ስምምነት” በመባል የሚታወቀውና ለዩክሬይን የእህል ምርት መተላለፊያ የሚፈቅደውን አሠራር ታግዳለች።

ሩስያ በመርከቦቿ እና በመድህን ዋስትና አገልግሎት ተጠቃሚነቷ ላይ የተጣሉት እገዳዎች “የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ እንዳትልክ እንቅፋት ፈጥረዋል” ብትልም ካለፈው ዓመት አንስቶ ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴ ወደ ውጭ መላኳ ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG