በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያለው የጸጥታ ችግር፣ በሰብአዊ ርዳታ አቅርቦቶች ላይ እክል እየፈጠረ እንደኾነ፣ የአደጋ ስጋት እና ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሺፈራው ተክለ ማርያም፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የመሥሪያ ቤታቸውን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ የጸጥታ ችግር ለሥራቸው ዕንቅፋት እንደኾነባቸው ገልጸዋል፡፡
አስቸኳይ ድጋፍ ለሚሹና ከስምንት ሚሊዮን በላይ ለሚደርሱ ዜጎች ሊቀርብ የሚችል በቂ የእህል ክምችት እንዳለ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት መድረስ ያልተቻለባቸው ቦታዎች መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም