ሥጦታው የተበረከተው አግራ በአፍሪካ ሃገሮች የሚሠራውን አነስተኛ ይዞታ ያላቸው ገበሬዎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ነው፡፡
አግራ ተቀማጭነቱ አፍሪካ ውስጥ የሆነ፣ አንድ ፅ/ቤት ናይሮቢ - ኬንያ፣ ሌላ ፅ/ቤት አክራ - ጋና ያለው አፍሪካ መር ተቋም ነው፡፡
የአግራ ዋነኛ ተግባሩ የአነስተኛ ገበሬዎችን ገቢ በማሣደግ አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ ምርታቸውን በማበረታታት በአፍሪካ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ከተለያዩ አጋሮች፣ ከአራሾችና ከአርብቶ አደሮች ጋር መሥራት ነው፡፡
አግራ በቅርቡ የጀመረው አዲስ መርኃ ግብር "የዳቦ ቅርጫት" ብሎ በሚጠራቸው ሃገሮች ውስጥ አነስተኛ አራሾችን ይደግፋል፣ ያበረታታል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ፡፡