በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ሕብረት ሞሮኮን ከ30 ዓመታት በኋላ በአባልነት ተቀበለ


የሞሮኮ ንጉስ ሙሐመድ ስድስተኛ
የሞሮኮ ንጉስ ሙሐመድ ስድስተኛ

ምንም እንኳ ሽግግሩ ቀላል ባይሆንም፣ በዚህ ውስብስብና ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም፣ «የተባበረች አፍሪካ» አስፈላጊ መሆኗን፣ መሪዎቿ ተናግረዋል። ነገሩን ያወሳሰበውም፣ ሞሮኮ ቀድሞውንም ከዓመታት በፊት ከሕብረቱ የተለየችበት ውዝግብ ስላልተፈታ መሆኑ ታውቋል።

ሞሮኮ እአአ በ1948 ዓ.ም ከሕብረቱ የተለየችው፣ የአፍሪካ ሕብረት ለምዕራባዊ ሰሐራ ነፃነት እውቅና ሲሰጥ መሆኑ ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሞሮኮ ምዕራብ ሰሐራን «ግዛቴ ነች» ስትል ቆየች፣ ምዕራብ ሰሐራም የአፍሪካ ሕብረት አባል እንደሆነች አለች። የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ትናንት ሰኞ ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ “ቤተሰብ ሲጠናከርና ሲበዛ፣ እንደ ቤተሰብ ማሰብና መፍትሔም መፈለግ እንችላለን” ብለዋል።

ሞሮኮ ያለ አንዳች ለምሳሌ ምራዕብ ሰሐራ «ካልተመለሰችልኝ» የሚል ዓይነት ቅድመ ሁናቴ ሳታስቀምጥ ወደ ሕብረቱ መቀላቀሏ፣ የሞሮኮ መንግሥት ሰላማዊ ሽግግር መፈለጉን የሚያመለክት መሆኑ ተመልክቷል።

የአፍሪካ መሪዎች በሰጡት አስተያየትም፣ ሞሮኮ ሕብረቱን ለመቀላቀል ያደረገችው ውሳኔ፣ በአንድነትና በሰላም መካከል ያለ የምርጫ ውጤት ነው ብለዋል።

«አፍሪካ ሀገሬና ቤቴ ነች፣ ከረዥም ጊዜ በኋላ ወደ ቤት መመለስን የመሰለ አስደሳች ነገር የለም» ያሉት ደግሞ፣ ንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ ናቸው።

ሞሮኮ፣ ከ54 የሕብረቱ አባላት፣ የ39ን የዩሁንታ ድምፅ አግኝታ ነው ወደ ሕብረቱ የተቀላቀለችው።

XS
SM
MD
LG