በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት የአፍሪካ ሀገሮች ያቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ያሉት ሦስት የአፍሪካ ሀገሮች በያዝነው ሳምንት ያቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ በአፍሪካ ዙሪያ የሰላም ጥብቃ ተግባር ኃላፊነት የአፍሪካ ህብረት እንዲሆን ሳያደርግ አይቀርም።

በተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ያሉት ሦስት የአፍሪካ ሀገሮች በያዝነው ሳምንት ያቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ በአፍሪካ ዙሪያ የሰላም ጥብቃ ተግባር ኃላፊነት የአፍሪካ ህብረት እንዲሆን ሳያደርግ አይቀርም።

የውሳኔውን ሀስብ ያቀረቡት ኢትዮጵያ፣ ኢኳቶርያል ጊኒና ኮት ዴቯር ሲሆኑ እንደ ሁኔታው እየታየ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአፍሪካ ህብረት ለሚመሩ የሰላም ጥበቃ ተልዕኮዎች ገንዘብ እንዲያቀርብ ይጠይቃል።

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ያሉትን የሰላም ጥበቃ ኃይሎችን የሚያንቀሳቅሰው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሲሆን ባጀቱ የአፍሪካ ህብረትን ያራቁታል ተብሏል። ይህ በተለይ ጎልቶ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ሶማልያ ውስጥ አል ሸባብን በሚታገልበት የምስራቅ አፍሪካ ክፍል ነው።

የውሳኔው ሃሳብ ከፀደቀ ቢያንስ ለወደፊቱ የሚኖሩት የሰላም ጥበቃ ተልዕኮዎች ጽህፈት ቤቱ አዲስ አበባ በሆነው የአፍሪካ ህብረት ሥር ይተዳደራሉ ማለት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG