በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ኤርትራ በአዲስ አቅጣጫ ለመጓዝ የደረሱበትን ውሳኔ የአፍሪካ ሕብረት አፀደቀ


ፎቶ ፋይል፡- የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሚ
ፎቶ ፋይል፡- የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሚ

የኢትዮጵያና ኤርትራ መሪዎች ለሁለት አሥርት ዓመታት የዘለቀውን አለመግባባት አስወግደው በአዲስ አቅጣጫ ለመጓዝ የደረሱበትን ውሳኔ የአፍሪካ ሕብረት አፀደቀ፡፡

የኢትዮጵያና ኤርትራ መሪዎች ለሁለት አሥርት ዓመታት የዘለቀውን አለመግባባት አስወግደው በአዲስ አቅጣጫ ለመጓዝ የደረሰበትን ውሳኔ የአፍሪካ ሕብረት አፀደቀ፡፡

ሁለቱ ሀገሮች በአጨቃጫቂው ድንበራቸው ምክንያት እአአ በ1998 ጦርነት ከአካሄዱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የኤርትራ ልዑካን ቡድን ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባን መጎብኘቱ ይታወሳል፡፡ ከጦርነቱ በኋላ የሁለቱ መንግሥታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችም ተቋርጠው ቆይተዋል፡፡

የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባለፈው ወር ሲናገሩ ከዚህ ቀድሞ የተደረሱ የሰላም ስምምነቶችን በሙሉ አከብራለሁ ብለዋል፡፡

የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሚ ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ

“ግንኙነቶችን ለማሻሻል በኢትዮጵያና በኤርትራ መሪዎች በተወሰዱ ዕርምጃዎች ከልብ ተደስተናል” ብለዋል፡፡

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ትናንት ይህን አስተያየት የሰጡት ሞሪታንያ ላይ በተካሄደው 31ኛው የአፍሪካ መሪዎች መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

“የአፍሪካ ሕብረት የማያወላውል ድጋፍ አላችሁ” ሲሉም ፖል ካጋሚ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ መሪዎች ቃል ገብተዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG