በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሂዩማን ራይትስ ዋች ለአፍሪካ ህብረት ያቀረበው ጥሪ


Human Rights Watch
Human Rights Watch

የአፍሪካ ህብረት ነገ ሰኞ ለሚከፈተው የአፍሪካ ሰብዐዊ እና ህዝባዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባዔ ድጋፉን እንዲሰጥ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ ። ነገ የሚከፈተው የኮሚሽኑ ጉባዔ የዚህ እየተገባደደ ያለው የአውሮፓ 2021 ዐመተ ምህረት የመጨረሻው ስብሰባ ነው።

የሰብዐዊ መብት ቡድኑ ሂዩማን ራይትስ ዋች ባወጣው መግለጫ የአፍሪካ ህብረት በኮሚሽኑ ስድሳ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ " ኢትዮጲያን ጨምሮ አህጉሪቱ ውስጥ ስር እየሰደዱ ላሉ የሰብዐዊ መብት እና የዲሞክራሲ ቀውሶች መፍትሄ እንዲፈልግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

አስከትሎም"ኢትዮጵያ ውስጥ በተለየም እየተባባሰ እና እየተስፋፋ ባለው ውጊያ የሚደርሱት በደሎች እና ጉዳቶች ክትግራይ ክልል አልፈው በተሰፋፉበት ባሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ጠንካራውን የሰብዐዊ መብት መስፈርትና ደንቦቹ በአባል ሀገሮች ማስከበር አለበት" ብሏል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር ካሪን ናንቱሊያ በሰጡት ቃል " በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካው ዘርፍ እና በአህጉራዊ የሰብዐዊ መብት ተቋማት መካከል እየሰፋ ያለው ክፍተት በሰብዐዊ መብት በአያሌ አሰርት የተገኙ ክንዋኔዎች የማፍረስ አደጋ ደቅኑዋል " ሲሉ አሳስበዋል።

አህጉራዊው ህብረት ሱዳን እና ቻድን በሚመለከትም ሁለቱን ጠንካራ የሆኑ ህገ መንግስት እንዲሁም ዲሞክራሲ እና ምርጫዎች የሚመለከቱትን ሕግጋቱን ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም ብለዋል።



XS
SM
MD
LG