በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሙሳ ፋኪ አፍሪካ ህብረትን ሰለገነቡት ቻይናውያን


የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ
የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ

በፒዮንግቻንጉ የክረምት ኦሎምፒክስ ዋዜማ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ወዳጃዊ ንግግር መፈጠሩን እንደምትደግፍ ቻይና አስታወቀች።

በፒዮንግቻንጉ የክረምት ኦሎምፒክስ ዋዜማ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ወዳጃዊ ንግግር መፈጠሩን እንደምትደግፍ ቻይና አስታወቀች።

የቻይና የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ዋንግ ዛሬ ቻይና ቤይጂንግ ውስጥ ለጋዜጠች በሰጡት መግለጫ የንግግሮቹና ድርድሮቹ መቀጠል አጣብቂኙን ለመፍታትና ባህረ ገቡን አካባቢ ይወረሰውን መጥፎ አዙሪት ለመስበር ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በጋራ ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባዔ፣ የቻይና የግንባታ ሰራተኞች አዲስ አበባ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት በኢንተርኔት መሰለያ አስገብተውበታል ተብሎ የወጣውን ሪፖርት፣ ግንኙነቶቻችን ለምናጋት የተፈፀመ ሪፖርት ነው ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

ቻይና ጽህፈት ቤታንን ትሰልላለች ብየ አልጠረጥርም ያሉ ሙሳ ፋኪ ከተልዕኳችንና ከቻይና ግንኙነታችንን ጋር ለማጠናከር ካለን ፍላጎት የሚያዛንፈን ተግባር አይኖርም ብለዋል።

የፈረንሳይ ጋዜጣ ለሞንድ ስማቸው ያልተገለፀ የህብረቱ ባለሥልጣናት ጠቅሶ፣ ባለፈው ወር ባወጣው ዘገባ ቻይና በሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር የገነባቸውን የአፍሪካ ህብረት ህንጻ መሰላያ መሳሪያዎች ጠቅጥቃበታለች ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG