በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ2018 የክረምት ኦሎምፒክስ አፍሪካውያን ይሳተፋሉ


ኤርትራዊው ሻነን አበዳ
ኤርትራዊው ሻነን አበዳ

የ2018 የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድሮች ዛሬ ደቡብ ኮሪያ ፒዮንግቻንግ ውስጥ አንጸባራቂ በሆነው የብርሃን ትዕይንትና የአትሌቶች ሰልፍ በይፋ ተጀምሯል። ዘንድሮ ናይጄሪያ የሴቶች የበረዶ የገበቴ ቅምጥ ሸርተቴ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳልፋለች። በረዶው ላይ በሰዓት መቶ ሃምሳ ኪሎ ሜትር ፍጥነት ሽው ብለው ይነጉዳሉ።

የ2018 የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድሮች ዛሬ ደቡብ ኮሪያ ፒዮንግቻንግ ውስጥ አንጸባራቂ በሆነው የብርሃን ትዕይንትና የአትሌቶች ሰልፍ በይፋ ተጀምሯል።

ዘንድሮ ናይጄሪያ የሴቶች የበረዶ የገበቴ ቅምጥ ሸርተቴ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳልፋለች። በረዶው ላይ በሰዓት መቶ ሃምሳ ኪሎ ሜትር ፍጥነት ሽው ብለው ይነጉዳሉ።

በዘንድሮው ውድድር ታሪክ የሚሰሩ ሌሎችም የትውልድ መሰረታቸው አፍሪካ የሆኑ አትሌቶች አሉ። ካናዳ ውስጥ ከሚኖሩ ኤርትራውያን የተወለደው ሻነን አበዳ ኤርትራን ወክሎ የመጀመሪያ የበረዶ መንሸራተት ስፖርት ይወዳደራል፡፡

አክዋሲ ፍሪምፖንግ ከጋና በትንሽ መንሸራተቻ በረዶ ላይ መንሸራተት፤ ሲሚዴሌ አዴግቦ ደግሞ የናይጄሪያ የመጀመሪያ የዚሁ ዘርፍ ሴት ተወዳዳሪ ሆና ቀርባለች።

ጋና ተወላጅዋ ማሚ ቢኒ የዩናይትድ ስቴትስ ፈጣን ስኬቲንግ ቡድን ውስጥ ተሰልፋለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG