በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መሪዎች ነጻ የንግድ ቀጠና ለመመሥረት እየሠሩ ነው


የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት - አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት - አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ከ17 ዓመታት ድርድር በኋላ የአፍሪካ መሪዎች ብዙ ተስፋ የተጣለበትን አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ከሦስት ዓመት ለመመሥረት ወስነው ነበር፡፡

መሪዎቹ አዲስ አበባ ላይ ለዓመታዊ ጉባኤ በሚገናኙበት በዚህ ወቅትም ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመተርጎም እጅግ አዳጋች እንደሆነባቸው ነው፡፡

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና በአፍሪካ ካሉ 55 አገሮች ውስጥ ከኤርትራ በስተቀር 54ቱ ተሳታፊ ናቸው፡፡

የሥምምነቱን ተግባራዊነት ለማፋጠን መሪዎቹ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይመክራሉ፡፡

ነጻ የንግድ ቀጠናው ታሪፍን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በማስወገድ በ2034 በአፍሪካ የውስጥ ንግድን 60 በመቶ ለመጨመር ያለመ ነው፡፡ ይህም 1.3 ቢሊዮን ያላት አህጉርን ድምር የአገር ውስጥ ምርት 3.4 ትሪሊየን ዶላር ያደርሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፍሪካ አገራት እርስ በእርሳቸው የሚገበያዩት ንግድ መጠን 15 በመቶውን ብቻ ነው። ከአውሮፓ አገራት ጋር ግን 65 በመቶ የሚሆነውን ንግድ ይፈጽማሉ።

የዓለም ባንክ እንደሚለው ውጥኑ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ 50 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካውያንን ከድህነት አረንቋ በማውጣት በ2035 ገቢያቸውን በ9 በመቶ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

ወደ ተግባር ለመግባት ግን ጋሬጣ ገጥ ሟቸዋል፡፡ የታሪፍ ቅነሳን በተመለከተ ሥምምነት ላይ አለመድረስና በኮቪድ 19 ምክንያት ድንበራቸው መዘጋቱ ከችግሮቹ ጥቂቶቹ ናቸው።

የቢሮክራሲ ማነቆና፣ የአንዳንድ አገሮች ከልክ ባለፈ ንግዳቸውን አልስነካም ማለት ለታሰበው ነጻ የንግድ ቀጠና ምሥረታ እንቅፋት እንደሚሆን ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG