በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መሪዎች ጽንፈኝነትን በብቃት ለመቋቋም አዲስ ስልት እንዲነደፍ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ

ሰኞ ሚያዚያ 14/ 2016 ዓም በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ላይ የተሰበሰቡት የአሕጉሪቱ መሪዎች ይበልጥ እየተባባሰ በመጣው የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ መክረዋል።

ከተሰብሳቢዎቹም መካከል ሽብርተኝነትን ለመከላከል ክልላዊ ተጠባባቂ ኃይል እንዲቋቋም የጠየቁት የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኒቡ ናቸው። ጉዳዩን አስመልክቶ ውስብስብ ችግሮች መኖራቸውን አምነው፣ ከዓለም አቀፍ ሕጎች እና ከሀገራት ብሄራዊ ሉዓላዊነት ጋራ የተጣጣመ ግልጽ ሥልጣን ያስፈልጋል’ ሲሉ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፡ የመንግሥታቱ ድርጅት ውስን ስኬት ላገኙት ተልዕኮዎች ብቻ የሚያወጣው በቢሊዮኖች የሚሰላ ገንዘብ፣ ሽብርተኝነት እየተስፋፋባቸው ባሉት የአፍሪካ ሀገራት የአስፈላጊ ግብአቶች እጥረት ስጋት እንዳሳደረባቸው ተናግረዋል።

የሁኔታውን አሳሳቢነት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሃመድ፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2023 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሽብር ጥቃቶች ሳቢያ የተገደሉት ሰዎች ብዛት ከዚያ በፊት ከነበረው በ22 በመቶ ከፍ ብሎ 8 ሺህ 352 ደርሷል ብለዋል።

ይህም እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2017 ዓ.ም ወዲህ ከፍተኛው ደረጃ ላይ መድረሱን እና በሳህል የተዘገበው አሃዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሽብር ሳቢያ ከተገደሉ ከፊል ያህሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሳህልን፣ ሶማሊያን እና ሞዛምቢክን ጨምሮ በአፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ከእስላማዊ መንግሥት እና ከአልቃይዳ ጋራ ቁርኝት ያላቸው ቡድኖች በሲቪሎች እና በወታደራዊ ኃይሎች ላይ የተነጣጠሩ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ መቆየታቸው ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG