በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሜሩን ጋናን 2 ለ 0 አሸንፈች

የካሜሩን ቡድን
የካሜሩን ቡድን

በጋቦን አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ለፍፃሜ የሚጋጠሙት ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ ታውቀዋል፡፡

በጋቦን አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ለፍፃሜ የሚጋጠሙት ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ ታውቀዋል፡፡

ካሜሩን ጋናን 2 ለ 0 አሸንፋ ትናንት ቡሩኪና ፋሶን 4 ለ 3 ከሸኘው የግብፅ ቡድን ጋር ለዋንጫው ፍፃሜ ትጋጠማለች፡፡

ለደረጃ ቅዳሜ ቡሩኪናና ጋና ይጫወታሉ፡፡

በዛሬው ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ብልጫ ያሳየውና ሁለት ድንቅ ጎሎችን ያስቆጠረው የካሜሩን ቡድን ነው፡፡

የፍፃሜ ግጥሚያዎች የሚካሄዱት በዋናዋ ከታማ ሊብረቪል ስቴዲየም ይሆናል፡፡

XS
SM
MD
LG