ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ አሁን ባላቸው የንግድ ሥርዐት የብሪክስ አባል መኾን ቢችሉ እንኳን፣ “አባልነቱ በራሱ የሚያስገኝላቸው ቀጥተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የለም፤” ሲሉ፣ የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ ገለጹ፡፡
ጥምረቱ በመገንባት ላይ ያለው ዐቅም፣ የዓለምን የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ኅብረት፣ ባለሁለት ዋልታ እንደያደርገው የጠቆሙት፣ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪው ዶክተር ግዛቸው ዐሥራት ደግሞ፣ “አፍሪካውያን ሀገራትም፣ ብሔራዊ ጥቅማቸውን መሠረት አድርገው ተጠቃሚ የሚኾኑበትን መንገድ ከወዲሁ ማበጀት ይኖርባቸዋል፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡
መድረክ / ፎረም