በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካዊ ቱጃር ታንዛኒያ ውስጥ ተጠለፉ


መሃመድ ዴውጂ
መሃመድ ዴውጂ

የታንዛንያ ፖሊሶች በአፍሪካ ከሁሉም ወጣቱ ቢሊዮነር ቱጃር የሚባሉት ሰው መጠለፋቸውን ተከትሎ የዋና ከተማዋን የዳሬሰላምን እና ዙሪያዋን ድንበሮች ዘግተዋል።

የታንዛንያ ፖሊሶች በአፍሪካ ከሁሉም ወጣቱ ቢሊዮነር ቱጃር የሚባሉት ሰው መጠለፋቸውን ተከትሎ የዋና ከተማዋን የዳሬሰላምን እና ዙሪያዋን ድንበሮች ዘግተዋል።

የአርባ ሰባት ዓመቱ መሃመድ ዴውጂ ትናንት ሃሙስ ጠዋት የአካል እንቅስቃሴ ስፖርት ሊሰሩ ወደ አንድ ሆቴል ሊገቡ ሲሉ ጨንበል ያጠለቁ ሁለት ታጣቂዎች እንደጠለፉዋቸው የዳሬሰላም ፖሊስ አዛዥ ላዛሮ ማምቦሳሳ ገልፀዋል።

ኮሎሲየም ሆቴል እና የስፖርት ክለብ የሚገኘው ኦይስተር ቤይ በሚባለው የዳሬሰላም የባለለፀጎች አካባቢ ነው -የፖሊስ አዛዡ እንዳሉት ታጣቂዎች ወደሰማይ ከተኮሱ በኋላ ዴውጂን አፋፍሰው መኪና ውስጥ አስገብተው ተፈትልከዋል። ፖሊሶች ዋና ተጠርጣሪዎች ያሏቸውን ሁለት ነጮች እየፈለጉ ናቸው።

እኚህ ባለጸጋ በአሥር ሃገሮች በግብርና በመድን ዋስታና በትራንስፖርትና እና የምግብ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰራው /METL/ ግሩፕ የተባለው ኩባኒያ ባለቤት ሲሆኑ ከሁለት ዓመታታ በፊት ፎርብስ መጽሄት የሃብታቸው መጠን እንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አውጥቶ ነበር፡፡ ለእኚህ ሰው መጠለፍ “ኃላፊ ነኝ” ያለ ወገን እስካሁን ብቅ አላለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG