በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የመሬት ኪራይ፣ ግብርናና ምግብ


Goita, Mammadou. Executive Director, IRPAD (Bamako, Mali)
Goita, Mammadou. Executive Director, IRPAD (Bamako, Mali)

በአፍሪካ የመሬት ኪራይ የምግብ ዋስትና እንደማይሰጥ አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡

የመሬት አጠቃቀምና በዓለምአቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለው መንግሥታት “ኪራይ” የሚሉት፣ የሚቃወሙት ተሟጋቾች ደግሞ “የአፍሪካን መሬት መቀራመት” የሚሉት አያያዝ የአፍሪካን ግብርና ሊጎዳ እንደሚችል አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡

ሌሎች ደግሞ የምግብ ሰብል በዓለም ላይ የተትረፈረፈ እንዲሆን ስለሚያስችል ዋጋውን ያወርደዋል፤ የዓለምን የምግብ ዋጋም ያረጋጋል ብለው ያስባሉ፡፡

አንዳንድ ተከራካሪዎች እንደሚሉት በርግጥ ሃገሮቹ ወደውጭ በተለይ ወደአፍሪካ እየዘለቁ መሬት የሚከራዩት ሕዝቦቻቸውን ለመመገብ ነው፤ እነርሱ በቂ ወይም ለም መሬት፣ የራሴ የሚሉት የተትረፈረፈ የምግብ ሰብል ምርትም የላቸውምና፡፡ ሌሎች ደግሞ “መሬትን በሌሎች ሃገሮች የሚይዙት እንደማንኛውም ሸቀጥ ነው” ይላሉ፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡XS
SM
MD
LG