በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት የምግብ ዋስትናን አላረጋገጠም


የአፍሪካ መንግሥታት በቂ የፖለቲካ ዝግጁነት እንዲኖራቸው መፍትሄው ሩቅ አይደለም፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው የአፍሪቃ የ2012 ሰብዓዊ ልማት ሪፖርት “ረሃብን በቁጥጥር ሥር በማዋል ብቻ በአፍሪቃ ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ ይቻላል” ይላል።

ለዚህም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የአህጉሪቱ የልማት አጀንዳ ማዕከል መሆን ይኖርበታል።

ሪፖርቱ ዛሬ ከቀትር በፊት በአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ይፋ ሲደረግ በኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ዩጂን ኦዉሱ “ባለፉት ሰላሣ ዓመታት የአፍሪቃ መንግሥታት የህዝቦቻቸውን ፍላጎት ቢከተሉ ኖሮ ይህ ሪፖርት አስፈላጊ ባልሆነ ነበር…” ብለዋል።

ኦዉሱ በተጨማሪም “ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚኖረው ሰው ሩብ የሚሆነው በምግብ እጦት አይሰቃይም ነበርም” ብለዋል።

“የአፍሪቃ መንግሥታት የህዝቦቻቸውን ፍላጎት እውን ቢያደርጉ ኖሮም አፍሪቃ የምግብ ዋስትናን ባረጋገጠች ነበር…” ሲሉ አክለዋል።

ዝርዝሩን ከመለስካቸው ዘገባ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG