በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ


አፍሪካ ዛሬ ሰኞ በይፋ በተጀመረው የአህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነት አማካይነት የሰላምና የብልፅግና ምዕራፍ ልትያያዝ እንደምትችል ተገለፀ።

ትናንት ኒጀር ላይ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የአህጉሪቱ ቁጥር አንድ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ናይጄሪያ እና ቤኒን የነፃ ንግድ ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን ኤርትራ ብቸኛዋ ስምምነቱን ያልተቀላቀለች ሃገር ሆናለች።

ስምምነቱ ከተሳካ የሦስት ነጥብ አራት ትሪሊዮን ዶላር ነፃ ንግድ ቀጣና በመፍጠር የሥራ እና የልማት ዕድሎችን እንደሚከፍት ኤክስፐርቶች ተንብየዋል።

ትናንት ዕሁድ ስምምነት የተከናወነው አስራ ሰባት የፈጀ ብርቱ ድርድርና ጭቅጭቅ ከተካሄደ በኋላ ሲሆን እንደኤክፐርቶቹ ትንበያ በአፍሪካ ሃገሮች መካከል የሚካሄደውን የንግድ እንቅስቃሴ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በስድሳ ከመቶ ያሳድገዋል።

ይሁን እንጂ አህጉሪቱ አስተማማኝ መንገዶች እና የባቡር መስመሮች እጥረት ወይም ጨርሶ አለመኖርሁከት፡ ሙስና እና ሥር የሰደደ ቢሮክራሲን የመሳሰሉ በርካታ ፈተናዎች የተደቀኑባት መሆኑዋ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG