በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ (ድንቅነሽን) ሉሲን ሲጎበኙ - አዲስ አበባ - ሐምሌ 27/07/15
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ (ድንቅነሽን) ሉሲን ሲጎበኙ - አዲስ አበባ - ሐምሌ 27/07/15

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። የዛሬው ፕሮግራማችን የተለያዩ ጋዜጦች ስለ ፕረዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት በጻፉት ላይ ያተኩራል።

የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ስላካሄዱት ጉብኝት የዘገበው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ገዢው ፓርቲና ወጋኞቹ የምክር ቤት መቀመጫዎችን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠሩበት ሁኔታ ፕረዚዳንት ኦባማ ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያን መንግስት በዲሞክራስያዊ መንገድ የተመረጠ ብለውታል ይላል።

የሰብአዊ መብት ቡድኖች ፕረዚዳንት ኦባማ ለውጥ እንዲደረግ እንዲገፉ የጠየቁ ቢሆንም ፕረዚዳንቱ በይፋ ባደረጉት ንግግር ለዘብ ማለቱን መርጠዋል። ኢትዮጵያ ለዘመናት ያህል በንጉሰ-ነገስታዊና በፍጹማዊ አገዛዝ ስር የነበረች ሀገር እንደመሆንዋ መጠን ለሀገሪቱ ያላቸውን አክብሮትና የተደቀኑባትን ተግዳሮቶች በሚገባ እንደሚረዱ ጫና ካደረጉ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ለተቃዋሚዎች ቦታ እንዲሰጥ በተለሳለሰ መልክ ጥሪ አድርገዋል ሲል ዘገባው ጠቁሟል።

“የኢትዮጵያን ታሪክ በሚገባ እንረዳለን። ያለፈችበት ችግርንም እናውቃለን። ህገ-መንግስት ተመስርቶ በዲሞክራስያዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት እንዲኖር ያደረገበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ገና ብዙ መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን ለመቀበል ቀዳሚው ይመስሉኛል” ማለታቸውን፣ ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቅሷል።

በዋሽንግተን የሁማን ራይትስ ዋች ስራ አስኪያጅ Sara Margon፣ በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደው ምርጫ ዲሞክራስያዊ አልነበረም። በርግጥ በምርጫው እለት ብጥብጥ ወይም አይን ያወጣ የድምጽ ስርቆት አልነበረም። ሆኖም በመሰረታዊ መብት ላይ ያለው ጭቆና፣ ኢትዮጵያውን የሚመስላቸውን ተናግረው፣ በሰላም ለመኖር የሚችሉ መስሎ እንዳይሰማቸው አድርጓል ሲሉ መናገራቸውን ጽሁፉ ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው፣ በሀገሪቱ ያለው ስርአት መሻሳል እንደሚያስፈልገው ይገነዘባሉ ካለ በኋላ ጽሁፍ፣ ያሉትን ጠቅሷል። “ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ ዲሞክራሲ ነው። ለምዕተ-አመታት ዲሞክራስያዊ አሰራርና ባህል ካልነበረባት ሃገር እየወጠን ያለን መሆናችን፣ መዘንጋት የለበትም። ስለሆነም በጥቂት አስርተ-አመታት፣ የኛን ጉዳይ ከውሰድን ደግሞ፣ በሁለት አስርተ-አመታት ውስጥ፣ የዲሞክራሲ አሰራር ችግሮችን ሁሉና የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች ሁሉ፣ እናስወግዳለን ማለት አይደልም። ነገር ግን ትክክለኛውን መንገድ ይዘናል የሚል እምነት አለን። ለህዝባችንና ለብልጽግና ስንል፣ ማክበር የሚገባን ህገ-መንግስታዊ ዲሞክራሲ አለን” ማለታቸውን፣ ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቁሟል።

--------

የጋርዲያን ጋዜጣ ድረ-ገጽ ደግሞ ፕረዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያው ጉብኝታቸው ወቅት የሰው ልጅ አያት የሆነችውን ሉሲን ጎብኝተዋል። ሉሲ ስለ ፕረዚዳንት ኦባማም ሆነ ስለ United States የምታውቅወ ነገር የለም። ፕረዚዳንት ኦባማን ስታይም የተናግረችው ነገር የለም ይላል። ለፈገግታ ያህል ማለት ነው።

የ 3.2 ሚልዮን አመት እድሜ ያላት ሉሲ የምትገኘው በኢትዮጵያ ብሄርውዊ ቤተመዘክር ሲሆን ባለፈው ሰኞ ፕረዚዳንት ኦባማ እንዲያይዋት ወደ ብሄራዊ ቤተመንግስት እንደተወሰደችና ፕረዚዳንት ኦባማ ከአጥንቶችዋ እንዱን በእጃቸው እንዲነኩ እንደተፈቀደላቸው ጋርዲያን ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቁሟል። ኦባማ እጅግ በጣም ከመደነቃቸው የተነሳ ወደ ኋላ አብረዋቸው የተጓዙ የምክር ቤት አባላትን ይዘው እንደገና ሊያይዋት እንደተመለሱ የጋርዲያን ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ አውስቷል።

ፕረዚዳንት ኦባማ የሉሲን አጥንት እንዲነኩ ያበረታቱት ዶክተር ዘርኢሰናይ አለምሰገድ “የሉሲን አጥንት የሚነካ ማንም ሰው የለም። ሆኖም ልዩ የሆኑ ሰዎች ልዩ ተደራሽነት ያገኛሉ” ማለታቸውንም ዘገባው ጠቅሷል።

---------

ብሉምበርግ የዜና አገልግሎት ደግሞ ፕረዚድስንት ኦባማ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ከጂኦተርማል ማለት ከከርሰ ምድር ሀብት የኤለክትሪክ መብራት ሃይል ከሚያመነጭ ተቋም የመብራት ሃይል አቅርቦት ለመግዛት ስምምነት እንደፈረመ ጠቁሟል። ከጂኦተርማል መብራት ሃይል ለማመንጨት በህብረት ከሚሰሩት ኩባንያዎች አንዱ ከሆነው የአይስላንዱ Reykjavik ኩባንያም ጭምር እንደሆነ ገልጿል።

ስምምነቱ “ትልቅ ነገር” እንደሆነ የገለጹት Njoroge፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዩቹ ሶስት ወረት ውስጥ ቁፋሮ እንደሚጀር መግለጻቸውን ብሉምበርግ ጠቅሷል። Edward Njoroge ናይሮቢ ያለውን በርክሊ ኤነርጂ የተባለውን ኩባንያ ይወክላሉ። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።

አፍሪካ በጋዜጦች - የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ስላካሄዱት ጉብኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG