በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአፍሪካ የረሃብ ዓመት አለፈ - 2015


በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚያበቃው የአውሮፓ 2015 ዓመተ ምሕረት ለአብዛኛው የአፍሪካ አህጉር የረሃብ ዓመት ሆኖ ሊያልፍ ነው።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚያበቃው የአውሮፓ 2015 ዓመተ ምሕረት ለአብዛኛው የአፍሪካ አህጉር የረሃብ ዓመት ሆኖ ሊያልፍ ነው።

በምሥራቅ እና በደቡባዊ አፍሪካ የኤል ኒኞ የአየር ንብረት ክስተትና ሌሎችም የአየር ንብረት መዘበራረቅ ሁኔታዎች ከባድ የምግብ ቀውሶችን ቀስቅሰዋል።

ከሰሃራ በስተደቡብ ያለው የአፍሪካ ክፍል ከየትኛውም የዓለም አካባቢ የበዛ የረሃብ ተጋላጭ ያለበት መሆኑን ከአራት ሰው አንዱ በቂ ምግብ እንደማያገኝ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስገንዝቧዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ባወጣው መረጃ 10.2 ሚሊየን ሰው ለምግብ እጥረት መጋለጡን ተናግሯል፡፡

ግጭቶች በበረከቱባቸው በደቡብ ሱዳን፣ በመካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክና በሳህል አውራጃ ሃገሮች ውስጥ ድኅነት መባባሱና የህዝብ ብዛት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡ ረሃቡን ከሚያበረቱት ምክንያቶች መሃል ተጠቅሰዋል።

አኒታ ፓወል ከጆሃንስበርግ - ደቡብ አፍሪካ ያጠናቀረችው እነዚህ የተለያዩ ቀውሶች ያላቸውን የጋራ ባህርይ የተመለከተችበት ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG