አዲስ አበባ —
ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ማጨስ የሚከለክለውን ሕግ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር መሻሻሎች አሉ ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በተለይ ለአንዳንድ የውጭ ዜጎች አዲስ ነገር እየሆነባቸው ነው፣ በሂደት ግን አየተለመደ ይሄዳል ብለዋል - በሚኒስቴር መሥራቤቱ የፖሊሲ አማካሪ ዳዊት ዲቃሶ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፡፡
በጤና፣ በሥነ ሕዝብና በመድሐኒት ቁጥጥር ላይ የሚመክር የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ በአፍሪካ ሕብረት የስብሰባ አዳራሽ ተጀምሯል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
-
እስክንድር ፍሬው