በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት ጀመረች


ፎቶ ፋይል፦ በክትባት ማዕከል ውስጥ ያሉ ሰራተኞች በኬፕ ታውን ላብራቶሪ ውስጥ እኤአ ኦክቶበር 5/2021
ፎቶ ፋይል፦ በክትባት ማዕከል ውስጥ ያሉ ሰራተኞች በኬፕ ታውን ላብራቶሪ ውስጥ እኤአ ኦክቶበር 5/2021

የደቡብ አፍሪካ መድሃኒት አምራች ፋብሪካ በአፍሪካ የኤምአርኤንኤ ኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒትን በማምረት የመጀመሪያው ሆኗል፡፡

መድሃኒቱ የተመረተው ሞደርና ይፋ ያደረገውን የህክምና መረጃዎችን መሰረት በማድረግ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የደቡብ አፍሪካው መድሃኒት አምራች የኮቪድ-19 ከትባቱ መድሃኒት በመጭው ኅዳር በሰዎች ላይ ሙከራ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፋብሪካው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች እንዲያመርት በዓለም የጤና ድርጅት የሚደገፍና እውቅና ከተሰጣቸው አምራች ድርጅቶ አንዱ መሆኑን ተነግሮለታል፡፡ አፍረጅን የተነሰኘው የዚህ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፔትሮ ተባላንስ የኤም አር ኤን ኤ ከትባት በድርጅቱ ባለሙያዎችና እውቀት የተሰራ ሲሆን ከሌላ አገር የተላለፈ ቴክኖሎጂ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሯ ከሞደርና አምራች ኩባንያ የማምረት ፈቃዱን የተጋሩ ቢሆንም ሞደርና እንዳለው ከድርጅቱ ጋር በአንድነትና ትብብር የሠሩ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በሌላ አገር ካሉ ሳይንቲስቶች ጋር በትብብር መስራታቸውንና ድጋፍ ማግኘታቸውን አልሸሸጉም

“ይህ እኛ የምንማርበት ቢሆንም በወጤቱ ግን በጣም በመደሰት ተገርመናል፡፡ ይሁን የመድሃኒት አሰራሩ ቀመር በዓለም ዙሪያ ባሉ ሳይንቲንስቶችና ባለሙያዎቹ አጋሮቻችን ይፋ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ የኛ ብቻ ሥራ አይደለም በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ ካሉ ተባባሪ ሳይንቲስቶች ጋር የተደረገ የህብረት ሥራ ውጤት ነው፡፡”

የደቡብ አፍሪካ የብሄራዊ የጤና መመሪያ ዋና ዳይዬክተር የመድሃኒት አምራቹ ድርጅት የሠራበትን ፍጥነት አድንቀው ይህ ለአገሪቱ ትልቅ ጠቀሜያ ያለው ተቋም በመሆኑን ከሳይንቲስቶችና ከድርጅቱ ጋር አብረው

XS
SM
MD
LG