በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መንግሥታት የኢኮኖሚ ቁጥጥራቸውን እንዲያላሉ ተጠየቁ


የንግዱ ህዋ ከተመቻቸላቸው መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ይመጣሉ

በአዲስ አበባ ከሚካሄደው የአፍሪቃ ንግድ ጉባዔ ጎን ለጎን በመንግሥታቱ ድርጅት በተጠራ ስብሰባ ላይ የተናገሩት የቀድሞ የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ቻርለስ ሳሉዶ “አህጉሪቱ እንድታድግ መንግሥታቱ የኢኮኖሚ ቁጥጥራቸውን ማላላት አለባቸው” ብለዋል።

ጉባዔው አህጉሪቱ ያላትን ዕምቅ ኃብትና ታላቅ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕድል ለውጭ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች የሚያሳይ ነው።

የቀድሞው የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ግን በእርሣቸው ልምድና ተሞክሮ የውጭ መዋዕለ ነዋይ ለመሳብ ብቻ የሚደረግ ጥረት ውጤቱ ውስን መሆኑን ጠቅሰው “አገሮች የሚጠበቅባቸው የንግድ ሥራን የሚያቀላጥፍ ፖሊሲ መዘርጋት ብቻ ነው፤ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ይመጣሉ” ብለዋል።

ሆኖም በአፍሪቃ ግዙፉና የመጀመሪያው ኃላፊነት የገንዘብ መዋቅር መዘርጋት እንደሆነ አሳስበዋል።

ዝርዝሩን ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG