ዋሺንግተን ዲሲ —
ዲጂታል ዴሞራክራሲ ደመወዛቸውን ሕዝብ የሚከፍላቸውን ሠራተኞችና ባለሥልጣናትን እንዲሁም መንግሥታትን የመፈተሻ፣ የመከታተያ፣ የመመርመሪያ አዲስ ዘዴ ሆኗል፡፡
ዌብ ሳይቶች፣ የሞባይል ስልኮችና ሌሎችም መገናኛ መሣሪያዎች አፖች በመላ አፍሪካ ዜጎች በፖለቲካው ውስጥ ይበልጥ በቅርበት እንዲሣተፉ እያስቻሏቸዡ ነው፡፡
ደካማ አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ከመጠየቅ አንስቶ የሙስና አድራጎቶችን ሹክ እስከማለትና እስከማጋለጥ ይደርሳል፤ ያ ሰፊ ተሣትፎ፡፡
በለት ተለት ሕይወት ውስጥም እንዲሁ! ክፍያዎችን እንደወትሮ ገንዘብ በቦርሣ ተሸክሞ እየቆጠሩ ሳይሆን በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከመፈፀም አንስቶ ታክሲና ምግብን እስከማዘዝ፣ ወዘተረፈ .....
በአፍሪካ ዲጂታል አብዮት እየተንሠራፋ ነው - በኮምዩኒኬሽንስ አማካሪዋ ታንዛኒያዊቱ ማሪያ ሳሩንጊ እምነት....
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ