በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ በኮቪድ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል


በደቡብ አፍሪካ የኮረና ቫይረስ ክትባት ሲሰጥ እኤአ ግንቦት 17 2021
በደቡብ አፍሪካ የኮረና ቫይረስ ክትባት ሲሰጥ እኤአ ግንቦት 17 2021

የአፍሪካ የበሽታና መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል በአህጉሪቱ ባላፈው ወር ውስጥ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የሚሞተው ሰው ቁጥር ወደ 17 ከመቶ ከፍ ማለቱን ዛሬ ሀሙስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ ማዕክሉ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጾ፣ አንዳንድ አገሮችም የሚያደርጉት ምርመራ ከሚያስፈልገው መጠን እጅግ ያነሰ መሆኑን በመግለጽ አስጠንቅቋል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕክል ኃላፊ ጆን ኒኮንጎሶንግ ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ በድረ ገጽ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው በሀምሌ ወር በአህጉሪቱ ስላለው የኮቪድ 19 ወረርሽ መጥፎ ገጽታማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ እንዲህ የሚለው ይገኝበታል

“በተጠቀሰው በዚህ ጊዜ ውስጥ የታየው ጭማሪ በአማካይ አራት ከመቶ ይሆናል፡፡ ባለፉት አራት ሳምንታት ውስጥ የሚሞቱ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ባላቸው አገሮች ውስጥ በአማካይ በ17 ከመቶ ማደጉን መዝግበናል፡፡ የኮቪድ ምርመራን በተመለከተ 58 ሚሊዮን ምርመራዎችን የተደረጉ ሲሆን ባላፈው ሳምንት ብቻ በአፍሪካ 1.3 ሚሊዮን ምርመራዎች ተደርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ ያ ቀደም ሲል ከነበረው ሳምንት በ19 ከመቶ ያነሰ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር አሁንም 11.2 ከመቶ ላይ እንደቆመ ነው፤፡

በአፍሪካ በኮቪድ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:37 0:00

በጠቅላላው በአሁጉሪቱ ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 239ሺ መድረሱን እና ባለፈው ሳምንት 6ሺ 700 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡ የሟቾቹም ቁጥር ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነጻጽር ተጨማሪ 700 ሰዎች የሞቱ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መለካከያ ማዕክል ለቫይረሱ መስፋፋት ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ የተደረጉ የዝርፊያ ክስተቶችና ወደ መካ የተደረገው የሙስሊሞች የኢድ አል ሀጅ ጉዞ አስተዋጽ ኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በመላው ዓለም ባለፉት ሳምታት ውስጥ እየተስፋፋ ነው የተባለውንና ከኮረና ቫይረሰ ዝርያዎች በተለላላፊነቱ የተለየ መሆኑን የተነገረለትን የዴልታ ቫይረስን በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ መሀመድ የሱፍ ከላከው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG