በአራት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ትላንት፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች በተባሉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታውቋል።
ከነዚህ መካከል አንዱ አንጋፋው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ዛሬ ወደ ሥራ መመለሱን ገልጿል፡
መድረክ / ፎረም