በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካና የቻይና ወዳጅነት


በቻይና የተሠራው የአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ሕንፃ
በቻይና የተሠራው የአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ሕንፃ

አፍሪካ ከነበረችበት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ የተነሣች መሆኑን የተናገሩ የአህጉሪቱ መሪዎች ቻይና ያደረገችውን አስተዋፅዖ አድንቀዋል።

ሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር ከወጣበት አዲስ ሕንፃ ምረቃ እስከ አፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ በነበሩ ሥነ-ሥርዓቶች የቻይና ተወካዮች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

አፍሪካ ከነበረችበት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ እየወጣች መሆኑ በተለያዩ ተናጋሪዎች በተገለፀበት መድረክ በዚህ ሂደት ውስጥ የእነርሱ አስተዋፅዖ ቀላል እንዳልሆነ ሲነገርም ቻይናዊያኑ አዳምጠዋል፡፡

አዲሱ ሕንፃ በተመረቀበት ሥነ-ሥርዓት ላይ የተናገሩት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይህንን ሃሣብ ካስተጋቡት መሪዎች ቀዳሚው ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥታ ለአዲሱ ሕንፃ ግንባታ የሰጠው መሬት በተለምዶ “ከርቸሌ” እየተባለ ይጠራ የነበረው ወሕኒ ቤት የነበረበት ሥፍራ ነው፡፡

ይህ ሥፍራ “ዓለም በቃኝ” ተብሎ ይጠራም እንደነበረ ያስታወሱት አቶ መለስ “የተስፋ መቁረጥና የተስፋ ቢስነትም ማሣያ ነበር” ብለዋል፡፡ የሃያኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የመጨረሻ አሥርት ዓመታትም “ለአፍሪካ ጥሩ አልነበሩም” ሲሉም አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

“በ‘ዓለም በቃኝ’ የነበሩት ታሣሪዎች በዚህ ዓለም ሕይወት ላይ ተስፋ እንደቆረጡ ሁሉ የተወሰኑ ሰዎችም በአፍሪካ ላይ ተስፋ ቆርጠው ነበር…” ብለዋል፡፡

አንዳንድ የታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራንም አፍሪካን ከድሕነትና ከትርጉም አልባ ብጥብጥ ሊያወጣት የሚችለው በድጋሚ በቅኝ ግዛት መያዝ እንደሆነ እስከመናገር ደርሰው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ዓለምአቀፉ መፅሔት The Economist “አፍሪካ ተስፋ ቢስዋ አሕጉር” የሚል ከጥግ እስከ ጥግ የሚነበብ ርዕስ ይዞ መውጣቱን በምሣሌነት ጠቅሰዋል፡፡

አፍሪካዊያንና መሪዎቻቸው ግን ትግላቸውን አጠናክረው በመቀጠላቸው ውጤቶች መታየት እንደጀመሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ እናም “አፍሪካ እያንሠራራች ነው” አሉ፡፡

ባለፉት ሦስት ቀናት በአፍሪካ ኅብረት ውስጥ የነበሩ የተለያዩ ስብሰባዎችንና ሥነ-ሥርዓቶችን የተከታተለውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG